የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በላቀ ትጋት ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለጸ

(EBC)- የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሰማዕታታን በመዘከር ሀገራዊ ግዳጅና ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በላቀ ትጋት ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ ተናገሩ፡፡

6ተኛውን የመከላከያ ቀን ምክንያት በማድረግ የባሩድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በሽራሮ የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

6ተኛው የመከላከያ ቀን ሲከበርም ሰማዕታቱን በማስታወስና ሁሌም ቆመውለት ለነበረው ዓላማ በፅናት መቆም አሁንም የሠራዊቱ ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ሊሆን እንደሚገባ ሜጀር ጀኔራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተሰው ሰማዕታት የኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት ቀጣይነት እንዲረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.