የደቡብ ክልል ከአንድ ሺህ 900 በላይ ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አንስቻለሁ አለ

አመራሮቹ የተነሱት ከ5 ሚሊየን ከሚልቅ ሕዝብ ጋር በተደረገ ውይይት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ደሴ ዳልኬ ተናግረዋል፡፡ ከ18 ሺህ በላይ የበታች አመራሮችም በዚሁ ርምጃ ከኃላፊነት ተነስተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 4 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ የገጠር መሬትና፣ 450 ሺህ የከተማ መሬት ከሙሰኞች እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡ በዚሁ ዓመት 15 ሚሊዮን የተመዘበረ ብርም እንዲመለስ ሆኗል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት 351 ሰዎች ህገ-ወጥ ቅጥር ፈፅመው ተገኝተው ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.