የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያደርጉት ክርክርና ድርድር በሚስተዋለው መጓተት ላይ እየተወነጃጀሉ ነው

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ለሚያደርጉት ክርክርና ድርድር በሚስተዋለው መጓተት ላይ እየተወነጃጀሉ ነው፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ኢሀዲግ ሆን ብሎ ድርድሩን እያዘገየ ነው ሲሊ ገዢው ፓርቲ ኢሀዲግ በበኩሉ እኔን ጠጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ድርድሩ በፍጥነት እንዲጀመር ፍላጎት አለኝ በሏል፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህዴግና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበው ለመመከርና ለመደራደር የጀመሩት የጋራ መድረክ ሁለት ወር አልፎታል፡፡በዚህ ጊዜ በሰነዱ ላይ ሳይግባቡ 6 ጉባኤዎች ያለውጤት ተጠናቀዋል፡፡ መድረኩ የድርድር ይሁን ወይስ የክርክር አልያም የውይይት የሚለው አንደኛው ያልተግባቡበት ጉዳይ ነው፡፡ 22ቱ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ድርድሩ፣ ክርክሩና ውይይተቱ ስለሚያዟቸው ዝርዝር ጉዳዮች ለመወሰን እስካሁን 6 ስብሰባዎች ቢያደርጉም የመግባቢያ ሰነዱ ወይም ቅድመ ደድርድሩና ክርክሩ አሁንም ገና አልተጠናቀቀም፡፡ ቅድመ ውይቱም ረጅም ጊዜ እየወሰደ ነው የሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡

ለዚህም ኢሀዴግ ሆን ብሎ ድርድሩን እያዘገየ ነው ሲሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይከሳሉ፡፡

 

ቅድመ ውይይቱን በፍጥነት ጨርሰን ወደ ዋናው ጉዳይ ለመግባት እንፈልጋለን የሚለው ኢህዴግ በበኩሉ ለመዘግየቱ እኔን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ባይ ነው፡፡ እናም መድረኩ እየተጓተተ ያለው በተቃዋሚ ፓርቲዎች ምክንያት ነው ሲል ይደመጣል፡፡

 

ፓርቲዎቹን ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል ስለአደራዳሪ ወይም አወያይ የተመለከተው   ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ተፎካካሪዎቹ መድረኩ በገለልተኛ ወገን ይመራ ባይ ናቸው፡፡ ኢህዴግ በበኩሉ 22ችንም ፓርቲዎች በየተራ መድረኩን መምራት እንችላለን የሚል አማራጭ አቅርቧል፡፡

 

የሆነው ሆኖ ሃሳቦቻችንን ወደ አንድ ለማምጣት አስቸጋሪ ቢሆንም ምክንያትና ሰበቦቻችንን ወደ ጎን አድርገን በአፋጣኝ ወደ ዋናው ድርድር መግባት እንፈልጋለን የሚሉ ፓርቲዎች አሉ፡፡

ለቅድመ ውይይት ብቻ 6 ጉባኤዎችን ያደረጉት ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከድርድሩ በፊት በውይይት ተሰላችተው ከመድረኩ ውጪ እንዳይሆኑ እየተሰጋ ይገኛል፡፡ድርድሩን በጉጉት የሚጠብቀው ህዝብም እሳካሁን ባለው መጓተት ተስፋ እንዳይቆርጥ ስጋት እንዳላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገልፀዋል፡፡


 

Leave A Reply

Your email address will not be published.