ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በዌስት ባንክ የምታካሂደውን የሰፈራ መርሀ ግብር ምክንያታዊ ማድረግ አለባት አሉ

ፕሬዝዳንቱ የእስራኤሉን ኤምባሲያቸውን ከቴላቪቭ ወደ ምስራቅ እየሩሳሌም አዛውራለሁ ያሉትን ሀሳብ በድጋሚ አጤነዋለሁ ብለዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙት ፍሊስጤሞች እስራኤል በግዛት ይገባኛል ጥያቀ ወደ ግጭት ካመሩ ጀምሮ ቀጣናው ውጥረት ተለይቶት አያውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜያትም የኦባማ አስተዳደር ስልጣን ከመልቀቁ በፊት እስራኤል በዌስት ባንክ የያዘችውን የሠፈራ መርህ ግብር እንድቆመ በፀጥትው ም/ቤት በተላለፈ ውሰኔ ላይ ዋሽንግተን ድምፀ ተአቅቦ ማድረጓ የታወሳል፡፡

በዚህም ሁለቱ ሀገራት ፍጥጫ ወዴት እንደሚያመራ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት ትንሿ ሀገር እስራኤል የቀዳችውን ማስፋፊያ እንድቆም ወስኖ ጉዳዩ አነጋጋሪ በሆነት ወቅት ዶናልድ ትራምፕ ለስራኤል አለሁላት በሚመስል ንግግር እኔ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆነው በኋላ ነገሮች ይለወጣሉ ብለው ነበር፡፡ ነገረ ስራቸው አወዛጋቢ ነው የሚባልላቸው ቢሊየነሩ ፕሬዝዳንት ትራምች ቃላቸውን ያጠፉ በሚመስል ሁናቴ አሁን የእስራኤል ማስፋፊያ ፕሮግራም ከፍልስጤም ጋር ለሚኖራቸው ሠላም ጥሩ አይደለም ብለዋል፡፡ እናም እሰኤል የምታደርገውን የሠፈራ ፕሮግራም በምክንያትና ውጤት ልታደርገው እንደሚባ ትራምፕ እስራኤል ሀዬም ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል፡፡ እናም ትራምፕ የኔታያሁ መንግስትን መርሃ ግብር ባልተጠበቀ መልኩ አውግዞታል፡፡

ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ከገቡ በላ ሣምንታት ውስጥ የስራኤልን የሠፈራ ፕሮግራም አስመልክተው ምንም ያሉት ነር አልነበረም፡፡ ከሰሞኑ ግን ትራምች የስራኤል ሠፈራ ለቀጣናው ጥሩ አይደለም ማለታቸው እያነጋገረ ነው፡፡ ትራምፕ ይህን ሲሉም የሠፈራፕሮግራሙ በሠላም ድርድሩ ጥሩ ነገር ነው ብዬ የማምን ሰው አይደለሁም በማለት ነው፡፡

ከዚህም ሌላ የአሜሪካን ኤምባሲ ከቴላቪቭ ወደ ምስራቅ እየሩሳሌም አዛውራለሁ ሲሉ የነበሩት ትራምች ጉዳዩን በድጋሚ አጤነዋለሁ ብለዋል፡፡ ትራምፕ ውሳኔው ቀላል ባለመሆኑ ኤምባሲውን የማዛወሩን ጉዳይ እንደገና ላየው መርጫለሁ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.