ዶ/ር ነገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ተሾሙ

(EBC)- ዶ/ር ይነገር ደሴ  አዲሱን ሹመት እስካገኙበት ጊዜ ድረስ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
አዲሱ ገዥ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት ሲያገለግሉ የቆዩቱን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን በመተካት ነው የተሾሙት፡፡
ከዚህ ቀደምም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩ ሲሆን፣ ሒልተን ሆቴልን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ሆቴሎች አስተዳደር አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቦርድ አባልም ሆነው ማገልገላቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ሹመቱ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እየተደረጉ ካሉ እንቅስቃሴዎች አካል ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.