ጋምቢያ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ቤት አባልነት አትወጣም አለች

አዲሱ የጋምቢያ ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው አገራቸው ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ቤት ICC አባልነት አትወጣም አሉ፡፡

በቀድሞው ፕሬዝዳንት የህያ ጃሜ ዘመን ጋምቢያ ከፍ/ቤቱ አባልነት እንደመትወጣ ሲገለፅ ነበር፡፡

ከረጅም ጊዜ ውዝግብ በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት አዳማ ባሮው ግን አገራቸው ከፍ/ቤቱ አባልነት እንደማትወጣ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

ባሮው ይህንን ያሉት የአውሮፓ ህብረት አመራሮች በጋምቢያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

የአፍሪካ ህብረት በቅርቡ በአዲስ አበባ ባካሄደው ጉባኤ፣ ከዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ለመውጣት በዛ ያሉ አራት መወሰናቸው ይታወቃል፡፡

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.