ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመቐሌ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ በመቐሌ ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዛሬ ማለዳ በመቐሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመቐሌ ቆይታቸው በሰማዕታት ኃውልት አዳራሽ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.