ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ዜና

በሀገራችን የተፈጠረዉን ሁከት እና ግርግር ለማረጋጋት የህዝቦችን ሰላም ለማስከበር ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታዉጆ ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።አዋጁን ለማስተግበርም በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ የጸጥታ ሀይሎች ተሰማርተው ግዳጃቻዉን በመወጣት ላይ ናቸዉ።

ይህን በሀገራችን አንዳንድ አካባቢወች የተፈጠረዉን ሁከት እና ግርግር እንደ ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር ሁኔታዉን ለማባባስ እና ለራሳቸዉ የጥፋት ስራ ለማዋል በሞያሌ አካባቢ የኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረዉ የገቡ የኦነግ ታጣቂወች ለመቆጣጠር እና ለመደምሰስ አንድ የሺ አለቃ ጦር በስፍራዉ ላይ ለግዳጅ ተሰማርቶ ይገኛል።ይሁን እንጂ የሺ አለቃዋ ጦር አዛዥ የሚገኝበት 5 የሺ አለቃዋ የሰራዊት አባላት የተሳሳተ መረጃ ይዘዉ ባደረጉት እንቅስቃሴ በአካባቢዉ ህብረተሰብ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በጉዳቱም የ9 ሰወች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰወች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።በአሁኑ ወቅት የሺ አለቃዋን አዛዥ ጨምሮ አምስቱም የሰራዊት አባላት ትጥቃቸዉን ፈተዉ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ የተደረገ ሲሆን የማጣራት ስራ እየተካሄደባቸዉ ነዉ። የማጣራት ስራዉን በአጭር ጊዜ ዉስጥ በማጠናቀቅም ዝርዝር ዉጤቱ ለህዝቡ የሚገለጽ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት አስታዉቋል።

በዚህ አጋጣሚ ለጠፋዉ ለሰዉ ህይወትና ጉዳት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

የስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት

Leave A Reply

Your email address will not be published.