የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ያስፀደቁት የካቢኒ አባላት ዝርዝር

(FBC) – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ያስፀደቁት የካቢኒ አባላት ዝርዝር
1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የግብርናና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር
2. አቶ ሲራጅ ፌጌሳ- የትራንስፖርት ሚኒስትር
3. ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ- የመንግስት ልማት ድርጅት ሚኒስትር
5. አቶ ኡመር ሁሴን- በሚኒስትር ማእረግ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
6. ወ/ሮ ኡባ መሀመድ- የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
7. ዶ/ር አምባቸው መኮንን- የኢንዱስትሩ ሚኒስትር
8. አቶ ሞቱማ መቃሳ- የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
9. ወ/ሮ ፎዚያ አሚን- ባህልና ቱሪዝም
10. አቶ አህመድ ሺዴ- በሚኒስትር ማእረግ የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
11. አቶ ዣንጥራር አባይ- የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
12. አቶ መለሰ ዓለሙ- የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስትር
13. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ- ጠቅላይ አቃቤ ህግ
14. ወ/ሮ ያለም ፀጋዬ- የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ሚኒስትር
15. አቶ መላኩ አለበል- የንግድ ሚኒስትር
16. ዶ/ር አሚር አማን- የጤና ጥበቃ ሚኒስትር

ዛሬ ሹመታቸው ከፀደቀ የካቢኒ አባላት መካከል 10 አዳዲስ አባላት ሲሆኑ፥ ስድስቱ ወደ ሌላ የሚኒስትርነት ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው።

—————————————–

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰጧቸው ተጨማሪ አዳዲስ ሹመቶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለዘጠኝ የፌደራል መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠታቸውን የሚኒስትሮች ምከር ቤት አስታወቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት፦

1. አቶ አባዱላ ገመዳ የጠቅላይ ሚኒስተሩ የብሔራዊ ደሕንነት ጉዳዮች አማካሪ፣

2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣

3. ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዩች ሚኒስትር፣

4. አቶ አህመድ አብተው በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣

5. አቶ ሞገስ ባልቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማእረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ፣

6. አቶ ዓለምነው መኮንን በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት፣

7. ዶክተር በቀለ ቡላዶ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪነግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፣

8. አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርማሽን መረብ ደሕንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና

9. አቶ ያሬድ ዘሪሁን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው ተሾመዋል።

ሹመቱም የትምህርት ዝግጅት እና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል።


ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል።

በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት በእጩነት ቀርበው የተመረጡት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ከቃለ መሃላው በኋላም ተሰናባቹ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ እና ተመራጯ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.