44 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል- የትምህርት ሚኒስቴር

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- 44 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤትም በተያዘው ወር መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግ የትምህር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዳኤታ ዶክተር ሳሙኤል ገልጸዋል።

የመቁረጫ ነጥቡ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥርና ሀገራዊ የመቀበል አቅም ላይ ተንተርሶ እንደሚወሰን ነው ዶክተር ሳሚኤል የተናገሩት።

በአሁኑ ጊዜም በሀገሪቱ የሚገኙ 44 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለመቀል የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዝግጅት እያከናውኑ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

የትምህረት ተቋማቱ ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ተማሪዎች ተቀብለው ያስተናግዳሉ ነው ያሉት ዶክተር ሳሙኤል።

በቀጣይ ዓመት ሰራ የሚጀምሩ ዘጠኝ አዳዲስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በ44 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያጠናቀቁ ይገኛል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የሀረማያና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲዎችም በቀጣይ ዓመት አዲስና ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናገረዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰንበቶ ቶማ፥ ተቋማቸው በመደበኛነት እያስተማራቸው ከሚገኙ ተማሪዎች በተጨማሪ ከ1 ሺህ በላይ አዳዲስ ተማሪዎች መቀበል የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቋል ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው ባሉት ሶስት የመማሪያ ካንፓሶቹ የሰው ሀይሉን አቅም በማሳደግ እና ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማማሏቱንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

በተለይም አዲስ ተማሪዎች ለመቀበል የተጀመሩ የማስፋፊያ ስራዎች መጠናቀቃቸውን የሚገልፁት ዶክተር ሰንበቶ፥ በዋናነት መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው ይገልፃሉ።

ከ32 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቀጣይ ዓመት በመደበኛ ተቀብሎ ለማስተማር እቅድ የያዘው የሀረማያ ዩኒቨርስቲም ያለውን ልምድ በመጠቀም አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርስቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ አለምእሸት ተሾመ ይናገራሉ።

በተያዘው ዓመት በሁሉም መስኮች የቤተ ሙከራ አቅርቦት ችግር እንዲፈታ በ284 ሚሊየን ብር የተገነባውን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት ግብዓት ግዥ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

ዩኒቨርስቲው የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅም በዋናት የመምህራን አቅም እያሳደግ እንደሚገኝ የሚገልፁት አቶ አለምእሸት፥ የስነ ማስተማር ዘዴ የሚከታተሉ ተማሪዎች ጨምሮ 5 ሺህ አዲስ ተማሪዎችን በተያዘው ዓመት ተቋሙ ይቀበላል ብለዋል።

በተያዘው ዓመት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመቀላቀል 285 ሺህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤታቸውን ያወቁ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.