ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በተገኙበት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

(ኤፍ ቢ ሲ)- የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው እለት 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በነገው መደበኛ ስብሰባ የሚገኙ ይሆናል። መረጃው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን መስጠቱ ተገለፀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ሹመቶች የተሰጡት የክልሉ የማስፈፀም አቅም ከፍ ለማድረግ ነው። በተጨማሪም የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የክልሉ መንግስት ለፌደራል መንግስት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ መሆኑንም…

ከንቲባ ድሪባ ያቋቋሙት ቦርድ ስለአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ጥያቄ አቀረበ

(ሪፖርተር)- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባለፈው ዓመት ፀድቆ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን ማስተር ፕላን አፈጻጸም እንዲያማክር ያቋቋሙት ቦርድ፣ የመጀመርያውን ስብሰባ ባካሄደበት ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ወሰን በግልጽ ይታወቅ ስለመሆኑ ጥያቄ ቀረበ፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ስብሰባ ከቦርድ አባላት ለተነሳው ጥያቄ ከንቲባ ድሪባ…

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ተቋም ተሸላሚ ሆነ

(ኢዜአ)- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የዓለም ዓቀፉ ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባኤ የ2018 የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ተቋም ተሸላሚ ሆነ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የሩዋንዳ አቻው ከምስራቅ አፍሪካ ለሽልማቱ ታጭተው የነበረ ሲሆን ኮሚሽኑ በቀዳሚነት የምስራቅ አፍሪካ ውጤታማ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ተቋም ሆኖ ተመርጧል። ዓለም ዓቀፉ…

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተስተጓጉሎ የነበረው በረራ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- ተስተጓጉሎ የነበረው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በረራ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱ ተነገረ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአሁኑ ወቅት የነበረው ችግር ተቀርፎ አውሮፕላኖች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን…

በአፍሪካ ነጻ የጋራ ንግድ ቀጠና ላይ የሚመክር የሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

(ኢዜአ)- በአፍሪካ ነጻ የጋራ ንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የፋይናንስ፣  የዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባኤ በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ''የአፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና ለስራ ፈጠራና ለኢኮኖሚ ብዝሃነት ያሉ የፋይናንስ አማራጮች" በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 3 እስከ 7 ቀን 2010 ዓ.ም በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።…

የንግዱን ዘርፍ ችግሮች ለመፍታት ባለሃብቶች ከመንግስት ጋር እንዲሰሩ ተጠየቀ

(ኢዜአ)-  የንግዱን ዘርፍ ችግሮች ለመፍታት ባለሃብቶች ከመንግስት ጋር እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ማምሻውን በንግዱ ዘርፍ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የንግዱ ማህበረሰብ ወኪል ከሆነው ከንግድ ዘርፍ ማህበራትና ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ከተለያዩ ድርጅቶች ባለቤቶች…

አሚሶም ከሶማሊያ ቀስ በቀስ የሚወጣበትን እቅድ አዘጋጀ

(ኤፍቢሲ)- የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ በሶማሊያ (አሚሶም) ከሀገሪቱ ጦሩን ቀስ በቀስ የሚያስወጣበትን እቅድ አዘጋጀ። የአሚሶም ከፍተኛ ኮማንደሮች በሞቃዲሾ ስብሰባ አካሂደዋል። ከውይይት በኋላ የአፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ፥ የእቅዱ ትግብራ ውጤታማ እንዲሆን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እና የተገኙ ለውጦችን እንደሚያጠና አስታውቋል። ይህ እቅድ ስኬታማ እንዲሆንም…

ኢትዮጵያና በተ.መ.ድ የሠላም ማስከበር እንቅስቃሴ ለመተባበር ተስማሙ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የሠላም ማስከበር ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ጂን-ፒየር ላክሮክስ ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይቱ ወቅት የኢትጵያና የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ ምክትል ዋና ፀሀፊው የኢትዮጵያ…

የኢትዮ- ሳዑዲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ

(ኤፍ ቢ ሲ)- 5ኛው የኢትዮ- ሳዑዲ ዓረቢያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ። በስብሰባው ላይ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ፥ ኢትዮጵያ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ለመሳብ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። ሳዑዲ ዓረቢያ አብዛኛውን የግብርና ምርቶቿን ከደቡብ አሜሪካ ሃገራት እንደምታስገባ የጠቀሱት ሚኒስትር ዲኤታው፥…