ዶ/ር ነገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ተሾሙ

(EBC)- ዶ/ር ይነገር ደሴ  አዲሱን ሹመት እስካገኙበት ጊዜ ድረስ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡ አዲሱ ገዥ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት ሲያገለግሉ የቆዩቱን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን በመተካት ነው የተሾሙት፡፡ ከዚህ ቀደምም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሃዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ እና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ

(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግጭት በተፈጠረባቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አካባቢዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በሃዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩ ይሆናል። ነገ ረቡዕ ደግሞ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት ከከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ።…

ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችል ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

(ኢዜአ)- በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ የአስተዳደር ወሰን ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችል ሁሉን አሳታፊ ኮሚሽን ሊቋቋም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። የሚቋቋመው ኮሚሽን ከየአካባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቀበል ስር-ነቀል መፍትሔ ይሰጣል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በአንዳንድ አከባቢዎች በተለይም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች…

ፓርላማው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማብራሪያ ጠራ

(ሪፖርተር )- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገሪቱ ወቅታዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ። ምንጮች እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በመጪው ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በምክር ቤቱ ተገኝተው ከሕዝብ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና…

በአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ኢህአዴግ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ዛሬ ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ሰልፈኞቹ፥ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትና የድምበር ኮሚሽን ውሳኔን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መቀበሉን በመቃወም ነው ሰላማዊ ሰልፉን ያካሄዱት። ነዋሪዎቹ በኢትዮጵያና ኤርትራ…

ሩሲያ ለኢትዮጵያ አምባሳደር ግሩም አባይ ሽልማት አበረከተች

(ኢዜአ)- የሩሲያ መንግስት የኢትዮጵያ ልዩ መልክተኛና ባለ-ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለነበሩት አምባሳደር ግሩም አባይ የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ሽልማት አበረከተ። በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴርጌ ላቭሮቭ ለአምባሳደር ግሩም የተሰጠው ዕውቅና የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር ባበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ተብሏል። ሽልማቱንም ከአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…

በወልቂጤ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ

(ኤፍ ቢ ሲ) በወልቂጤ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈቱ ሰማን እንዳሉት፥ በተፈጠረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። ከዚህ በተጨማሪም በግጭቱ በሰባት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱንም ተናግረዋል። በግጭቱ ሳቢያም በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና…

ኢትዮጵያ ከውሃ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

(EBC)- ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ኃይል በማመንጫት ቀዳሚ መሆኗን አለም አቀፉ የውሀ ኃይል ማመንጫ ማህበር አስታወቀ። ማህበሩ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በውሃ 3,822 ሜጋዋት በማመንጨት ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም አንጎላን በማስከተል ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች። ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ማህበሩ 6 ሺህ 450 ሜጋ…

ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3 እስከ 5 ያካሄደዉን አስቸኳይ ሰብሰባ አጠናቋል። ህወሓት/ኢህአዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትግልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባስቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፍን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና…

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ ተሾመለት

(EBC)- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ ተሾመለት የማህብሩ ስራ አስኪያጅ ሆና የተሰየመችው ወጣቷ ቤዛ ተስፋዬ ናት፡፡ በአፍሪካ የፔስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቁልፍ ሚና ካለቸው 13 ሴቶች አንዷ  የሆነችውና ስፔስ ጀነሬሽን የአፍሪካ አማካሪ  ምክር ቤት አስተባባሪ የነበረችው ቤዛ የኢትዮጵያን ስፔስ ስፔስ  ሳይንስ ሶሳይቲ እንድትመራ እድሉ ተሰጥቷታል፡፡…