በሃዋሳና ወልቂጤ ተፈጥረው በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል- የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- በደቡብ ክልል ሀዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች ተፈጥረው በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ። የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አህመድላዲን ጀማል ሰሞኑን በሃዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች መጠነኛ ግጭቶች ተከስተዉ እንደነበር ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል። በሃዋሳ የሲዳማ ብሄረሰብ…

ኢሃን መንግሥት ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት ፈጽሟል አለ

(ሪፖርተር)- በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በነበሩት ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) የሚመራው የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን)፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ታሪክ ይቅር የማይለው አገራዊ ክህደት መፈጸሙን አስታወቀ፡፡ ኢሃን ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያውያን ለተከታታይ ትወልዶች በከፈሉት መስዋዕትነት…

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ እየተከበረ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው። ትናንት በሀዋሳ ከተማ መከበር የጀመረው የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል ዛሬም በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ደምቆ እየተከበረ ይገኛል። በሲዳማ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ “የቄጣላ” ጨዋታና የፈረስ ጉግስን ጨምሮ…

ጅቡቲ የነበሩ 361 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

(ኢዜአ)- በጅቡቲ በስደት ላይ የነበሩ 361 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ስደተኞቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ በጅቡቲ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በተደረገው ጥረት መሆኑን ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላካው መግለጫ አስታውቋል። ስደተኞቹ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ በህገ-ወጥ…

መንግስት በየመን የባህር ዳርቻ በቅርቡ ህይወታቸውን ባጡ ኢትዮጵያዊያን ማዘኑን ገለፀ

(ኢዜአ)- የመንግስት ኮሙኑኬሽን ጉዳችዮች ፅ/ቤት በላከው መግለጫ መንግስት ባደረገው ማጣራት 100 ሰዎችን ጭና  ከሶማሊያ ቦሳሶ ተነስታ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በየመን ባህር ዳርቻ በደረሰባት አደጋ ሚያዚያ 29፣2010 ሰጥማ ከ60 በላይ  ኢትዮጵያዊያን ህይወት ማለፉንንና የደረሱበት አለመታወቁን ገልጿል፡፡ ጀልባዋ ከአቅሟ በላይ  ሰው በመጫኗ ነበር የመስመጥ አደጋ…

8ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- ባሳለፍነው እሁድ የተጀመረው 8ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው። በዛሬው እለትም የኢህአዴግ እና የኦህዴድ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ነው ኮንፍረንሱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው። በተጨማሪም የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦህዴድ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የኦህዴድ ስራ…

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና በትግርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና ትግርኛ ቋነቅ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የግዕዝና የትግርኛ ቋንቋን ስርዓተ ትምህርት ለማጽደቅ የሚያስችል መድረክ ተዘጋጅቷል። በመድረኩ ላይም ዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርሃ ግብሩን በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ መርሃ ግብሩ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሦስት ዓመታት የሚሰጥ…

የባድመ ከተማ ነዋሪዎች የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ከህዝቡ ጋር ውይይት እንዲካሄድ ጠየቁ

(ኤፍ ቢ ሲ)- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢትዮ - ኤርትራ ጉዳይ ይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም የባድመ ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትንና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን የተቃወሙት ነዋሪዎች ዛሬ ረፋድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች…

ሕወሓት አስቸኳ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

(ኢዜአ)- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/  አስቸኳይ ጉባኤ ትላንትበመቀሌ ከተማ  የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ተጀመረ። በዝግ የተጀመረው አስቸኳይ ጉባኤ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ  ድርጅቱ ከትላንት በስትያ ማምሻውን  ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው ጽሁፍ ገለልጿል። ኢትዮ – ኤርትራን አስመልክቶ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ድርጅቱ…

ኢትዮጵያ እና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በአዲስ መንፈስ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኤፍ ቢ ሲ)- ኢትዮጵያ እና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሁለቱን ሃገራት የመልማት ፍላጎት ባከበረ መልኩ በአዲስ መንፈስ በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ከትላንት በስትያ ካይሮ የገቡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር መክረዋል። መሪዎቹ በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽና…