ኢትዮጵያዊን ስደተኖችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የተመድ ባለስልጣናት ገለጹ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- ኢትዮጵያዊን ስደተኖችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የተመድ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው ጀልባዋ ሮዕቡ ጧት በኤደን ባህረ ሰላጤ አካባቢ የሰጠመች ሲሆን፥ የ46 ተሳፋሪዎች ህይወት መጥፋቱ ነው የተገለጸው። ከአደጋው ሰለባዎች መካከል 37 ያህሉ ወንዶች ሲሆኑ  ዘጠኞቹ ሴቶች  መሆናቸው…

አሜሪካ “C-130” የተባለ ወታደራዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ አበረከተች

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአሜሪካ መንግስት “C-130” የተባለ ወታደራዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ አየር ሀይል አበረከተ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ አውሮፕላኑ በትናንትናው እለት ነው በቢሾፍቱ ከተማ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል የተበረከተው። ወታደራዊ አውሮፕላኑ ርክክብ ላይም የአሜሪካ መንግስትን በመወከል በኢትዮጵያ…

የፍትህ ህግና ስርዓት ማሻሻያ ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

(ኤፍ ቢ ሲ)- የፍትህ ህግና ስርዓት ማሻሻያ ምክር ቤት ሊቋቋም መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ። የፍትህ ስርዓቱ በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡበትም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ዜጎችን ለእንግልት የፍትህ ስርዓቱን ደግሞ ለጥራት ችግር አጋልጦት መቆየቱን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተጠናው ጥናት ያመላክታል። ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት አለማግኘት እና…

ቮዳፎንና ኤምቲኤን በኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ገበያ ውስጥ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተዋል ተባለ

(EBC)- የደቡብ አፍሪካዎቹ ቮዳፎንና ኤምቲኤን ግሩፕ የቴሌኮም ተቋማት በኢትዮጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቁ፡፡ የቴሌኮም ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ መንግስት የቴሌኮም ዘርፍ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት እንደሚያደርግ በማስታወቁ በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የቴሌኮም ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት አላቸው፡፡ በመሆኑም ወደ ፊት ከኢትዮጵያ…

የንግድ ባንክና የልማት ባንክ የብድር ፖሊሲና አሠራር ለውጥ ተደረገ

(ሪፖርተር)- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረዥምና የመካከለኛ ጊዜ የፕሮጀክት ብድሮች መስጠት በማቆም የሥራ ማስኬጃ ብድሮች ብቻ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የፕሮጀክት ብድሮች እንዲሰጥ የተላለፈው ውሳኔ ታጠፈ፡፡ ውሳኔው ከሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ግንቦት 24 ቀን 2010…

በኢትዮ- ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የሃገራቱን ግንኙነት የሚያሻሽል ነው – ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

(ኤፍ ቢ ሲ)- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኢትዮ- ኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያሻሽል መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በተጀመረው 4ኛው ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጉባኤ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባሳላፈው ውሳኔ ላይ…

ክስ የተቋረጠላቸው ሁለት ባለሀብቶች ከውጭ ተመለሱ

(ሪፖርተር)- በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው ታዋቂ ባለሀብቶች መካከል ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሁለት ባለሀብቶች ወደ አገር ቤት ተመለሱ፡፡ በቅርቡ ክሳቸው የተቋረጠላቸውና ወደ አገር ቤት የተመለሱት ባለሀብቶች አቶ ጌቱ ገለቴና አቶ ገምሹ በየነ ናቸው፡፡ አቶ ጌቱ በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸው ተገልጾ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ከአገር መውጣታቸው የተነገረው፣…

የኢትዮጵያ መንግስት እይወሰዳቸው የሚገኙ የለውጥ እርምጃዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ተመድ ገለፀ

(ኢዜአ)- የኢትዮጵያ መንግስት አሁን እየወሰዳቸው ያሉ የለውጥ እርምጃዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ገልጿል። ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳቷም አድናቆቱን ገልጿል። የኢፌድሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በየካቲት ወር ያወጣው የስድስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ባሳለፍነው ቅዳሜ ባደረገው…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በኡጋንዳ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቅዳሜ በኡጋንዳ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለፀ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ጉብኝታቸው በ29ኛው የኡጋንዳ ብሄራዊ የጀግኖች በዓል እንደሚታደሙ ታውቋል። በዚህ ብሄራዊ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለአፍሪካ እና ለኡጋንዳ መልካም ስራ ለሰሩ ሰዎች ሀገሪቱ የምታበረክተውን ሜዳሊያ በፕሬዚዳንት ዮዌሪ…

ኢትዮጵያ የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነች

(EBC)- የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የሚከተለዉን ጥሪ አስተላልፏል። ለኢትዮጵያችን እድገትና ለሕዝቦች ተጠቃሚነት ሰላም ከምንም በላይ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡…