Browsing Category

News

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ገንቢ ውይይት የሚያደርግ ከፍተኛ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ ልትልክ ነው

(ኤፍ ቢ ሲ)- ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ገንቢ ውይይት የሚያደርግ ከፍተኛ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር፥ በድንበር ጉዳይ ላይ የሚነጋገር የሃገራቸውን ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ማሰባቸውን ተናግረዋል። በጃፓን…

በሞጆ ከተማ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው

(ሪፖርተር)- ከአዲስ አበባ ከተማ 76 ኪሎ ሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ አቅራቢያ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው፡፡ ለአካባቢያዊ ብክለት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን የቆዳ ፋብሪካዎች አንድ ቦታ ለማሰባሰብ የታቀደው ከዓመታት በፊት ቢሆንም ዕቅዱ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ልማት ኢንስቲትዩት ዋና…

አቶ ዘይኑ ጀማል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው ተሾሙ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- አቶ ዘይኑ ጀማል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው ተሾሙ። በቅርቡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው የተሾሙት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ባለባቸው የጤና እክል ምክንያት ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በግል ያቀረቡት ጥያቄ ማቅረባቸውና ተቀባይነት በማግኘቱ ተነግሯል። ይህንን ተከትሎም አቶ ዘይኑ ጀማል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር…

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያለምንም አድልኦና ወገንተኝነት ህዝብና አገርን ለማገልገል መዘጋጀቱን አስታወቀ

(ኢዜአ)- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያለምንም አድልኦና ወገንተኝነት ህዝብና አገርን ለማገልገል መዘጋጀቱን  ዋና ዳይሬክተሩ ጄኔራል አደም መሐመድ ገለጹ። አገልግሎቱን እንዲመሩ በቅርቡ የተሾሙት አመራሮች ዛሬ በአዲስ አበባ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አድርገዋል። በዚሁ ወቅት ጄኔራል አደም እንደገለጹት “ተቋሙ መንግስትንና ህዝብ የሰጠውን ተልዕኮ…

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአገራችን እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን አደነቀ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አልሁሴን በምክር ቤቱ 38ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአገራችን እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን አድንቀዋል፡፡ በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተነሳሽነት በአገራችን ለውጦች መምምጣታቸውን በመጠቆም፣ የህግ የበላይነት ከማስፈን፣ መሰረታዊ የሰብዓዊ…

ዶ/ር ነገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ተሾሙ

(EBC)- ዶ/ር ይነገር ደሴ  አዲሱን ሹመት እስካገኙበት ጊዜ ድረስ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡ አዲሱ ገዥ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት ሲያገለግሉ የቆዩቱን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን በመተካት ነው የተሾሙት፡፡ ከዚህ ቀደምም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሃዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ እና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ

(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግጭት በተፈጠረባቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አካባቢዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በሃዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩ ይሆናል። ነገ ረቡዕ ደግሞ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት ከከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ።…

ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችል ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

(ኢዜአ)- በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ የአስተዳደር ወሰን ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችል ሁሉን አሳታፊ ኮሚሽን ሊቋቋም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። የሚቋቋመው ኮሚሽን ከየአካባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቀበል ስር-ነቀል መፍትሔ ይሰጣል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በአንዳንድ አከባቢዎች በተለይም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች…

ፓርላማው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማብራሪያ ጠራ

(ሪፖርተር )- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገሪቱ ወቅታዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ። ምንጮች እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በመጪው ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በምክር ቤቱ ተገኝተው ከሕዝብ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና…

በአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ኢህአዴግ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ዛሬ ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ሰልፈኞቹ፥ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትና የድምበር ኮሚሽን ውሳኔን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መቀበሉን በመቃወም ነው ሰላማዊ ሰልፉን ያካሄዱት። ነዋሪዎቹ በኢትዮጵያና ኤርትራ…