Browsing Category

News

አዳዲስ የባቡር መስመር ፕሮጀክቶች ህልውናቸው በአበዳሪ ተቋማት ላይ የተመሠረተ መሆኑ ተጠቆመ

(ሪፖርተር)- በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብለው የታቀዱ አዳዲስ የባቡር መስመር ፕሮጀክቶች፣ ህልውናቸው በአበዳሪ ተቋማት ላይ የተመሠረተ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ…

ዓቃቤ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የቀረበው ክስ የተቀነባበረ ሳይሆን በማስረጃ የተደገፈ ነው አለ

(ሪፖርተር)- ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ እንዲደረግለት ጠየቀ ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሠረተባቸው ክስ እሳቸው በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ሲደረግባቸው በሰጡት ቃል መሠረት ሳይሆን ተቆራርጦ የተቀነባበረ መሆኑን፣ በቅድመ ክስ መቃወሚያቸው በመግለጽ ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቃወመ፡፡ የቀረበባቸው ክስ የተቀነባበረ ሳይሆን በማስረጃ የተደገፈ መሆኑንም ለፍርድ…

መንግሥት በነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ የማሻሻያ ዕርምጃዎች ሊወስድ ነው

(ሪፖርተር )- በርካታ ችግሮች ለሚታዩበት የኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ኢንዱስትሪ ዕድገት ያግዛሉ የተባሉ ዕርምጃዎች ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ ከተጋረጡበት በርካታ ችግሮች መካከል አንዱና ዋነኛው በቂ የነዳጅ ማደያዎች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች አለመኖር ነው፡፡ ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱት…

27 ህገ ወጥ ኤርትራዊያን ስደተኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

(ኤፍ ቢ ሲ)- ሲሚንቶ የጫነ በማስመሰል 27 ህገወጥ ኤርትራዊያን ስደተኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በጎንደር ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል። ከማይፀብሪ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ የተነሳው ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ እቃ መጫኛው ላይ ኮንቴይነር በመጫን እና ከላይ በላሜራ በመበየድ ከዚያም በላዩ ላይ ሲሚንቶ ይጭናል። ሙሉ በሙሉ ሲሚንቶ የጫነ በማስመሰልም…

የ52 ሺህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 67 ከመቶ ደርሷል

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የ52 ሺህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 67 በመቶ መድረሱን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀረጎት አለሙ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በዋናነት ፓኬጅ ሁለት የተባሉት 52 ሺህ 651 ቤቶች በአሁኑ ወቅት የግንባታቸው አፈፃፀም 67 በመቶ ደርሷል። ሰኔ ወር ላይም…

ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር በአዳዲስ የኢኮኖሚ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላት -የሲንጋፖር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

(ኢዜአ)- ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር በአዳዲስ የኢኮኖሚ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲዮ ጂ ሂያን ገለጹ። በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ የጀመሩት የሲንጋፖር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲዮ ጂ ሂያን ቀደም ብሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተነጋግረዋል። ሚስተር ዲዮ ጂ  ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ…

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል በተከሰሱ 23 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጠ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- በአዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ከልሎች ከ1996 አመተ ምህረት እስከ 2006 ዓ/ም የሃይማኖታዊ አላማ ለማራመድ በማቀድ የሸብር ተግባረ ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ 23 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ። ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ መድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኝነት ብይን የተበየነባቸው ተከሳሾች፤ 1ኛ እስማኤል በቀለ፣ 2ኛ ሱልጣን አሀመድ፣ 3ኛ አህመድ…

እንጀራ ከባእድ ነገሮች ጋር ቀላቅለው በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እየተጠናከረ ነው

(EBC)-እንጀራ ከባእድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ የሚደረግ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ የምግብ  የመድሃኒትና የጤና ክብካኬና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር  አቶ ጌታቸው ወረቴ  እንደተናገሩት ባለፉት 9 ወራት ብቻ በንፋስ ስልክ፣ በጉለሌና በኮልፌ ክፍለ ከተማ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ተይዘዋል፡፡…

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር አገኘች

(ኤፍ ቢ ሲ)- ኢትዮጵያ ለምርታማ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚውል ሁለት ነጥብ አራት ቢሊየን ብር ከዓለም ባንክ በብድር አገኘች። የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ ዳይሬክተር ካሮላይን ተርክ ስምምነቱን ፈርመዋል። ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አድማሱ እንደተናገሩት፥ የብድር ስምምነቱ ለምርታማ ሴፍቲኔት መርሃግብር…

ሜቄዶኒያ የአዛውንቶች እና የአዕምሮ ህምሙና መርጃ ማዕከል ለድርጅቱ ገቢ ታስቦ ያዘጋጀው የሎቶሪ ዕጣ ወጣ፡፡

ሽልማቱ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት የተዘጋጀ ነበር፡፡ ዳማስ መኪና፣ሳምሰንግ ጋላክሲ ሞባይሎች፣ ሳይክሎች፣ ፍላት ስክሪን ቴሌቪዢኖች ለተሸላሚዎች ተበርክተዋል፡፡ ለዚህ ስራ መሳካትም ብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም ምንም ዓይነት ክፍያ ከድርጅቱ እንዳልተቀበሉ ተገልጿል፡፡ ከ 1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች እየረዳ የሚገኘው ድርጅቱ ከመንግስት በተሰጠው 30 ሺህ…