Browsing Category

News

የህዳሴው ግድብ ሁለት ዩኒቶች በዚህ ዓመት ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ

(ኢዜአ)- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች በዚህ ዓመት ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምሩ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት ግድቡ ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 16 ዩኒቶች አሉት። ከነዚህ ዩኒቶች መካከልም ሁለቱ ኃይል ማመንጨት የሚያስችሉ ግብዓቶች እየተገጠመላቸው መሆኑን…

ኢትዮጵያና ጅቡቲ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚኒት ለማሳደግ ተስማሙ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የሁለቱ አገራት የጋራ የድንበር አስተዳደሪዎች የአገራቱን ህዝቦች የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚኒት የበለጠ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን ለማከናወን ተስማምተዋል። የአገራቱ የጋራ የድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ በአፋር ክልላዊ መንግስት ሰመራ ከተማ ከመጋቢት 3 - 5/2010 ዓ.ም ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት ተጠኗቋል፡፡ ይህን አስመልክቶ የውጭ…

መርማሪ ቦርዱ በይፋ ስራ ከጀመረ ወዲህ ከህብረተሰቡ 50 ጥቆማዎች የደረሱት መሆኑን ገለፀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በይፋ ስራ ከጀመረ ወዲህ ከህብረተሰቡ 50 ጥቆማዎች የደረሱት መሆኑን ገለፀ። የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋ እንደገለፁት፥ በአብዛኛው ጥቆማዎቹ ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የቀረቡ ናቸው። በቦርዱ ስልጣን ስር የሚወድቁ ጥቆማዎች ለኮማንድ ፖስቱ በማቅረብ ክትትል እንዲደረግባቸው እየተደረገ…

በአገሪቱ በቂ የነዳጅ ክምችትና አቅርቦት መኖሩ ተገለጸ

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)- በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በቂ የነዳጅ ክምችት መኖሩንና ምንም ዓይነት እጥረት አለመፈጠሩን የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ድረገፆች፤ የነዳጅ እጥረት አጋጥሟል፣ ዋጋ ሊጨምር ነው እንዲሁም ነዳጅ ሊጠፋ ነው በሚል የሚናፈሰውን መረጃ በተመለከተ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ…

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በመጋቢት ወር መጨረሻ ካርቱም ላይ ይወያያሉ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የሶስትዮሽ ውይይት በያዝነው መጋቢት ወር መጨረሻ ይካሄዳል። በሱዳን መዲና ካርቱም እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ውይይት በየካቲት ወር ሊካሄድ ታቅዶ ለሌላ ጊዜ በተዘዋወረው መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ከውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውጭ…

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ከሞጆ ደረቅ ወደብ ጋር መገናኘት በአጭር ጊዜ ውጤት እያስገኘ ነው

(ኢዜአ)- አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ከሞጆ ደረቅ ወደብ ጋር በተገናኘ በሁለት ወር ጊዜ ከሁለት ሺህ በላይ ኮንቴነሮችን ከውጭ ወደ ወደቡ ማመላለስ እንዳስቻለ ተገለፀ። የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበርና የኢትዮጵያ ባህርና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የባቡር መስመሩ ከወደቡ ጋር መገናኘት ለአገሪቷ የኢኮኖሚ እድገት አንድ…

አየር መንገዱ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ማእከልነቷን እንድታስቀጥል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለፀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ማእከልነቷን አስጠብቃ እንድትቀጥል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። 130 ኤምባሲዎች እና 40 አለም አቀፍ ድርጀቶችን ኢትዮጵያን መቀመጫቸው ያደረጉ ሲሆን፥ በሀገሪቱ ያለው ምቹ እና ቀልጣፋ የአየር ትራንስፖርትም ሀገሪቱን ተመራጭ አድርጓታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፥ አየር መንገዱ…

ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ለኦሮሚያ ተፈናቃዮች የገነባውን 121 ቤቶች አስረከበ

(ሰንደቅ)- ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በኦሮሚያና በሶማሌ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች መጠለያ የሚሆኑ በቢሾፍቱ ከተማ የገነባቸውን 121 ቤቶችን ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም ለከተማ አስተዳደሩ አስረከበ። የቤቶቹን ቁልፍ ለቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ገነት አብደላ ያስረከቡት ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ናቸው። ቴክኖሎጂ ግሩፑ…

ከመተማ ወደ ጎንደር ከተማ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

(ኢዜአ)- ከመተማ ወደ ጎንደር ከተማ በድብቅ በኩል ሊገባ የነበረ 21 ሽጉጦችና ከ15 ሺህ በላይ ጥይት መያዙን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ በጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ የሰራባ ኬላ አስተባባሪ ኮሎኔል ብርሃነ መብራት ለኢዜአ እንደተናገሩት የጦር መሳሪያና ጥይቶቹ የተያዙት ከጭልጋ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሰራባ…