Browsing Category

News

ኦህዴድ በዞን በከተማ አስተዳደሮችና በወረዳዎች አዳዲስ የአመራር ምደባ እያደረገ ነው

(የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በዞን፣ በከተማ አስተዳደሮችና በወረዳ  ደረጃ አዳዲስ የአመራር ምደባ በማድረግ ላይ መሆኑን የኦህዴድ  የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ። ኦህዴድ በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።…

ቤንሻንጉል ክልል ተፈናቀሉ የተባሉትን አላውቅም ሲል መግለጫ ሰጠ

ቤንሻንጉል ክልል ተፈናቀሉ የተባሉትን አላውቅም ሲል መግለጫ ሰጠ። የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ሃላፊ መልስ አልሰጥም አሉ። በገዛ ሀገራቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ህፃናቱን ይዘው ባህርዳር ቤ/ክርስትያን ደጃፍ ኑሯቸውን ቀጥለዋል። https://youtu.be/VDK3bwzzaL0

ዶክተር ፍቅሬ ማሩን ጨምሮ የ62 ተካሳሾች ክስ እንዲነሳ ተወሰነ

(ETHIO FM 107.8)- የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ፍቅሬ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾችን የክስ ሂደት ማንሳቱን አስታወቀ። ተከሳሾቹ የወንጀለኛ መቅጫ ህግን አንቀጽ 464 እና 494 በመተላለፍ ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ ያለና እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው ናቸው። ኢዜአ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባገኘው መረጃ መሰረት በእነ አበበ የኋላ መዝገብ…

ኢትዮጵያ እና ቻይና የ250 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

(ኤፍ ቢ ሲ)- ኢትዮጵያ እና ቻይና የ250 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂን ተፈራርመውታል። ብድሩ የመቐለ ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ለሚተገበረው ፕሮጀክት ይውላል ተብሏል። ትናንት የተፈረመው የብድር ስምምነት…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ለመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሠጡ

ሹመቱ የተሰጠው የትምህርት ዝግጀትና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት በማስገባት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ተሿሚዎቹ ከግንቦት 2 ቀን 2010  ጀምሮ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተመልክቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ተሿሚዎቹ:- አምባሳደር ደግፌ ቡላ በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትህና የሕግ ምርምርና…

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃላፊነት ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ያካሄዱት የውጭ ግኑኙነት እና የዲፕሎማሲ ስራ ስኬታማ እንደ ነበር ተገለፀ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ በሶስት በጎረቤት አገራት የደረጉት ጉብኝት ስኬተማ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ትላንት በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል። ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኬንያ ያደረጉት ጉብኝት ውጤታማ እና ወዳጅነቱን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን ትብብራችን ወደ ላቀ…

የአማርኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል በሱዳን ሊከፈት ነው

(አብመድ)- የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የገዳሪፍ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ የአረብኛ እና የአማርኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ሊከፍቱ ነው፡፡ ሁለቱ የድንበር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጎለብቱ ስራዎችን ፤ለመስራት የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ጎንደር ላይ ተፈራርመዋል፡፡ በጋራ ድንበር ላይ የሚኖረውን ህዝብ በጋራ ቋንቋ እንዲግባባ ያደርጋል…

‘ፋኦ’ ሚስተር ዴቪድ ፈሪን በአዲስ አበባ የክፍለ አህጉሩ አስተባበሪ አድርጎ ሾመ

(ኢዜአ)- ፋኦ ከህዳር 10 እስከ 17 ቀን 1998 ዓ.ም በጣልያን ርዕሰ መዲና ሮም ባካሄደው 33ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያ የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ መቀመጫ እንድትሆን መወሰኑ የሚታወስ ነው። ቢሮውም መጋቢት ወር 2000 ዓ.ም ተከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ሚስተር ዴቪድ ፊሪን ፋኦ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ…

የሚድሮክ ጎልድ የለገ ደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ታገደ

(EBC)- በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን የሚገኘው የሚድሮክ ጎልድ የለገ ደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከግንቦት 1/2010 ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ገልጿል። የሚድሮክ ጎልድ ለገ ደምቢ የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለብን ነው በማለት ቅሬታ በማንሳቱ ነው ሚኒስቴሩ ለጊዜው ፍቃዱን…

የኤርትራና ሶማሊያ ማዕቀብ ክትትል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ነው

(ኤፍ ቢ ሲ)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ እና ሶማሊያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተፈፃሚነት እንዲከታተል የተቋቋመው ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካዛኪስታን አምባሳደር እና የኮሚቴው ሊቀመንበር ኬይራት ኩማሮቭ የተመራው ኮሚቴ በሃገራቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዴት መሄድ እንዳለበት ለመምከር…