Browsing Category

News

የአማራ ክልል የሰላም ጉባኤ በባህር ዳር ተጀመረ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአማራ ክልል የሰላም ጉባኤ ዛሬ በክልሉ መዲና ባህር ዳር ተጀመረ። “አስተማማኝ ሰላም የህልውናችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። እንደዚሁም በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዎች የውጣጡ ተሳታፊዎች፣ የሀይማኖት…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ሃዋሳ ገቡ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ ክልል ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በወዋሳ ከተማ ይወያያሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዛሬ ጠዋት ላይ ሀዋሳ ከተማ የገቡ ሲሆን፥ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በቆይታቸውም በሃዋሳ ስታዲየም…

ዓለማቀፍን ዲጂታል ቤተ መፃህፍት ለመክፈት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አገር ሆና ተመርጣለች

(INSA)- አዲሱን ዓለማቀፍ ዲጂታል ቤተ መፃህፍት ለመክፈት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አገር ሆና ተመርጣለች፡፡ ቤተ መፃህፍቱ በሰባት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የተለያዩ መፃህፍት እንዲሁም ለእረፍት ጊዜ ንባብ የሚሆኑና በ3 የአፍሪካ ቋንቋዎች የተፃፉ የታሪክ መፃህፍት ይኖሩታል፡፡ በአሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ እንግሊዝና ሌሎች አገራት ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ዓለማቀፉ ጥምረት በኢትዮጵያ…

የአማራ ክልል ምክር ቤት ለስድስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጠ

(ኢዜአ)-  የአማራ ክልላዊ መንግስት  ምክር ቤት  ዋናና ምክትል አፈ ጉባኤን ጨምሮ ለስድስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጠ። በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቅራቢነት ከተሾሙት መካከል በፈቃዳቸው  በለቀቁት በአቶ ይርሳው ታምሬ ምትክ የምክር ቤቱን ምክትል አፈ ጉባኤ የነበሩትን ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞን ዋና አፈጉባኤ እና  ወይዘሮ ትልቅ ሰው ይታያልን ደግሞ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑት…

የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 29 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ

(Walta)- የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ ሥራ 29 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ ። ስድስት ወር በፊት የተጀመረውና በ16 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተካሄደ  ያለው የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ በአጠቃላይ የግንባታ ደረጃው 29 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጿል ፡፡ የኢንዱስትሪ መንደሩ የግንባታ አስተባባሪ አቶ አደራጀው መልኬ እንዳሉት የባህር ዳር ኢንዱስትሪ…

ኢትዮጵያ በትክክለኛ የፖለቲካ አቅጣጫ መሆኗን ተ.መ.ድ. ገለፀ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተ.መ.ድ) የሰብዓዊ መብት ኮምሽነር ዛይድ ራድ አልሁሴን ኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት በማምጣት ወደ ተለመደው ተፅእኖዋ ለመመለስ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኗን ገለፁ፡፡ ኮምሽነር ዛይድ ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ላይ እንደገለፁት በኢትዮጵያ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን የግንቦት ሰባት አባላት እጅ ሰጡ

(ኢዜአ)- በምዕራብ ጎንደር ዞን ከግንቦት ሰባትና ከኤርትራ መንግስት የጥፋት ተልዕኮ በመቀበል የሽብር ተግባር ይፈፅሙ የነበሩ ሰባት የቡድኑ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ምሕረት ጠይቀው ገቡ። የዞኑ አስተዳደር የፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ ይላቅ እንደገለፁት የቡድኑ አባላት የአካባበውን ሰላምና ደህንነት ለማወክ ከግንቦት ሰባትና ኤርትራ መንግስት ተልዕኮ በመቀበል…

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ረዳት ኃላፊ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ይገባሉ

(ሪፖርተር )- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተቀዳሚ ምክትል ኃላፊ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ለመምከር፣ ሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊው አምባሳደር ያማሞቶ ከጠቅላይ…

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በብሄራዊ ቤተመንግስት አሸኛኘት ተደረገላቸው

(ኢዜአ)- ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና የቀድሞዋ ቀዳማዊ እምቤት ሮማን ተስፋዬ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የወርቅና ከፍተኛ የክብር ዲፕሎማ ተበረከተላቸው፡፡ ትላንት በብሄራዊ ቤተመንግስት በተደረገ የሽኝት ፕሮግራም ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡ በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ…

በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በጫት ምርት ላይ ከነገ ጀምሮ ቀረጥ ሊጣል መሆኑ ተገለፀ፡፡

(አብመድ)- የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በጫት ምርት ላይ ከነገ ጀምሮ በተደራጁ ማህበራት አማካኝነት የቀረጥ ስራ ይጀመራል፡፡ በዋናነት ቀረጥ ማስቀመጥ ያስፈለገበትን ምክንያትም ሲገልፁ፤ በጫት ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የገዥን አቅም ማዳከምና ጫት የሚቅም ወጣትን ለመታደግ የታሰበ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ…